ጀግናው ፋኖ ተዘራ ጀንበር በሴረኞች ምክንያት ተሰዋ!

አሳዛኝ የስዋዕትነት ዜና

ሰኔ ፳፪፳፻፲፭ ዓ.ም
ሞዐ ሚዲያ – Moaa Media
ሸዋ – ሚኒሊካዊ
አዲስ አበባ – ጣይቱ
ኢትዮጵያ
https://t.me/Moamediamoresh

ከኦነግ ተልዕኮ የወሰዱ የመከላከያ አባላት ማክሰኝት ኬላ ፍተሻ ጣቢያ ላይ የፋኖ አማራ በጎንደር ቴዋድሮስ ብርጌድ አዘዞ ሻለቃ አባል የሆነው ፋኖ ተዘራ ጀምበር እና በምኒልክ ሻለቃ አባል አንድ ፋኖ በአጠቃላይ ሁለት የፋኖ አባላት በአሸባሪው የኦነግ መከላከያ ሃይል ተገደሉ።

የአማራን ህዝብ በጦርነት ለማንበርከክ እና ኢኮኖሚውንም ለማድቀቅ አልሳካለት ሲል አሁን ደግሞ ህግ ለማስከበር በሚል ምክንያት ያለማንም ከልካይ ኬላ ጣቢያዋችን አቁሞ ፤ የኦነግን ተልዕኮ የሚያስፈጽመው የኦነግ መከላከያ ሃይል፤ ህዝብን በጠራራ ፀሃይ በመረሸን ክልላችንን ወደ ለየለት ብጥብጥ እና ትርምስ እየከተተው ይገኛል።

ስለሆነም ህዝባችንም የተደቀነብህን የህልውና አደጋ እና ሴራ በሚገባ ተረድተህ ከፋኖ ጎን በመሠለፍ ፤ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ የተጋረጠብህን የህልውና አደጋ እንድትቀለብስ ጥሪ ቀርቧልሃል።

ለመላው የፋኖ አማራ በጎንደር አባላት እና ለመላው የፋኖ ወዳጂ የጎንደር ከተማ ህዝብ ፤ የአባላችን የፋኖ ተዘራ ጀምበር ስርዓት ቀብር የሚፈጸመው በደብረ-ታቦር ከተማ ስለሆነ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ወደ ደብረ -ታቦር የቀብር አሸኛኘት ስነ-ስረአት ስለሚደረግ በቦታው በመገኘት ስነ-ስርአቱን እንድትታደሙ እና ሌላኛው የፋኖ ጓዳችንንም ስርዐተ ቀብር እንድትታደሙ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን።

ለወዳጂ ዘመዶቻቸው ፤ ለትግል አጋሯቻቸውና ለመላው የአማራ ህዝብ ልባዊ መፅናናትን እየተመኘን ሁሉም የአማራ ህዝብ ለመጣው የህልውና አደጋ በተጠንቀቅ እንዲቆም በድጋሚ ለማሳሰብ እንወዳለን።

የነፃነት ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል!!

ድል ለአማራ ህዝብ!!!

“የፋኖ አማራ በጎንደር”
ጎንደር
ሰኔ 22/2015
https://t.me/Moamediamoresh

Discover more from wenchifEthiopia.com ወንጭፍ ኢትዮጵያ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading