የአርበኛ ዘመነ ካሴ ትውልድ አካባቢ እንደሆነች በሚነገርላት የመራይ ከተማ የዘር ፍጅት መፈፀሙን BBC አረጋግጧል።ኢሰመኮ ምርመራ ጀመርኩ ብሏል።

ዜና፡ #በአማራ ክልል #መርዓዊ ከተማ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ

በአማራ ክልል በሰሜን #ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ ሰኞ ጥር 20/2016 ዓ.ም በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተደረገ ውጊያን ተከትሎ በነዋሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ቤተሰቦች፣ ነዋሪዎች አና የዐይን እማኞች ተናገሩ።

ግድያው የተፈጸመው በቤታቸው እና በመንገድ ላይ በተገኙ ሰላማዊ ሰዎች ላይ መሆኑን ነዋሪዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባሕር ዳር ቢሮ በመርዓዊ ከተማ በንጹሃን ላይ ጥቃት እንደደረሰ ከተለያዩ ምንጮች መረጃው እንደደረሰው፣ ክትትል እና ምርመራም እያከናወነ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል።

ሰኞ ጥር 20/2016 ዓ.ም. ከጥቃቱ ቀደም ብሎ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ኃይሎች መካከል “ከባድ ውጊያ” እንደነበር የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ያንን ተከትሎ ከ100 እስከ 200 የሚደርሱ ሰዎች “ተረሽነዋል” ብለዋል።

ይህ ጥቃት የተፈጸመው ረፋድ አምስት ሰዓት አካባቢ የፋኖ ኃይሎች ከተማዋን ለቅቀው መውጣታቸውን ተከትሎ “መከላከያ ሠራዊት ቤት ለቤት በመዞር እና መንገድ ላይ ያገኛቸውን ሰዎች መረሸኑን” የተናገሩት የዐይን እማኞች፤ ጥቃቱ እስከ ምሽት አንድ ሰዓት የዘለቀ ነበር ብለዋል።
https://t.me/Moamediamoresh

Discover more from wenchifEthiopia.com ወንጭፍ ኢትዮጵያ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading