ይድረስ ለአማራ ዲያስፖራ

አርባ ቀን ወይስ 40 አመት? ከሞገድ እጅጉ(አማራ እንደ እስራኤላውያን)እስራኤላውያን 432 አመት በግብፅ ምድር በባርነት ተገዙ። እግዚአብሄር በመጨርሻው ወደ እነርሱ ሄደ። ከፈርኦኑም እጅ ነፃ ወጡ። ጉዞ ወደ ከነአን ተጀመረ። የአርባ ቀን ጉዞ ነበር። 40 ቀናት ብቻ! ነገር ግን የተስፋውዋን ምድር ለማየት 40 አመታት ፈጀ።ምን ተፈጠረ?“back to the wilderness” እንደገና ወደምድረበዳ ተመለሱ። የተሳካ ጉዞ ሊሆን ሲችል ይህ ጉዞ እንዴት ሊበላሽ ቻለ? ብለን ስንጠይቅ መልሱ ተስፋ፣ እምነት እና ፍቅር ማጣት ይሆናል ። ተስፋ የቆርጠ ሕዝብ በበረሀ ይቀራል። እምነትም የሌለው ሕዝብ በበረሀ ይቀራል። ፍቅርም የሌለው ሕዝብ በበረሀ ይቀራል።እኛ አማሮች እንደእስራኤላውያን ባርነት አላጋጠመንም። የፈርኦንም ሆነ የቄሳር ቀንበር አልተጫነብንም። ነገር ግን በራሳችን ባርነት ውስጥ ነው ያለነው። ራሳችን በሰራነው ባርነት ውስጥ ወድቀናል።እስራኤላይውያን አምነው ወጡ። ነገር ግን በጉዞው ላይ ፈጣሪያቸውን ሊኖሩት አልቻሉም። ወደኋላ እያዩ ወደ ምስር ምድር. . . እኛ የአማራ ተወላጆች የገጠመን አሁናዊ ሁኔታችን ይኸው ነው። በራሳችን የኔ እበልጣለሁ ባርነት ወድቀናል። ከፍ ሲል የኔ “ክልል” ዝቅ ሲል የኔ አውራጃ በሚል አስተሳሰብ ተጠልፈናል። ወያኔ አማራውን ጠባብ እና ጽንፈኛ ብሄርተኛ ለማድረግ 27 አመት ዳከረች። አልተሳካላትም። አማራው ላይ ያልተፈጸመ በደል የለም። ጭቆና፣ መድሎ ፣ መሳደድ መፈናቀል ፣ ተለይቶ መጠቃት አማራ ቢገጥመውም አንገቱን ቀና አድርጎ ትከሻውን ሰብቆ ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊ ዝቅ ሲል አማራዊ አስተሳሰቡን እሴቱን መጠበቅ ችሎ ነበር። እርግጥ ነው የተማረ መሪ ነበረን። ያወቀ መሪ ነበረን። መሪ ስንል ደግሞ የተመራመረ መሪ (caltvated in the intelectual level) ማለታችን ነው። እንደ ፕሮፌሰ አስራት ወልደየስ (አብዬ አስራት) ማለታችን ነው።አማራ መንግስታዊ ጥቃት የደረሰበት ከደርግ ጊዜ ጀምሮ ነው። ደርግ በአዋጅ አማራ እንዲገደል አድርጓል። በአዋጅ ሀብት ንብረቱን ዘርፏል። እንዲደኽይ አድርጓል። በስተመጨረሻም ደርግ ለወያኔ አቀብሏታል። ደርግ ፊውዳል በሚል የሽፋን ስም ሲፈፅመው የቆየውን ወያኔ ትህምትተኛ ብላ ቀጠለች። አማራ፦ በወያኔ ጊዜም ሀብት ንብርቱን ተነጥቆ እንዲኮሰምን ተደርጓም። መንግስታዊ መዋቅራዊ አድሎና መገለል (systemic political alienation )ተፈጽሞበታል። ለ27 አመት ግን አንገቱን ቀና አድርጎ ትከሻውን ሰብቆ ወያኔን ተታግሎ አሸንፎታል ብሎ 27 አመት ተታግሎ ያመጣው አብዮት ታዲያ በራሱ በአማራው የፖለቲካ ብስለት ማጣት በኦሮሞ ብልጽግና ማደናገርና ማሳመን (confused & convince) በሚባል ከኦሮሙማ ጋር ብቻ በሚገኝ ስሁት ፖለቲካዊ እሳቤ ተታልሎ ከፖለቲካ ጭዋታው ውጭ ተደርጎ እለት በእለት እየታረደ ይገኛል። ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል አይደል ተረቱበሌላ መልኩ መሪ ያጣ ህዝብም ሆኗል።ፕሮፌሰር አስራትን ሸኝተን ዶ/ ር በለጠ ሞላን አየን። የእሳት ልጅ አመድ ማለት ይህ ነው። አዎ የወያኔን መዋቅራዊ ጥቃት አማራው ቀለበስኩ ሲል አሁንም እዚያው የለመደው መከራ ውስጥ ነው። ይባስ ብሎ በነብሰ በላው ዘራፊውና ስግብግቡ የአብይ አህመድ ድራጎናዊ አገዛዝ እጅ ወድቆ የአፓርታይድ መዋቅር ተዘረጋበት። በ2013 ሀምሌ ወር የአማራ ህዝብ የአብይን መንግስት በቃኝ አለ። ፋነነ…ፋኖ ተሰማራ። በ17 ወራት ውስጥ ምንም የውጭ ድጋፍ ሳያገኝ የአማራ መስተዳድር ከተሞችን ተቆጣጠረ። ገጠሩን በጠቅላላ ተቆጣጠረ። እስራኤሎች 40 ቀን ሆናቸው። ወደ ከነአን ተቃረቡ። ሆኖመ‍እ አምላካቸው ወደ ነበሩበት የሲና በረሀ፣ የቀይ ባህር መዳረሻ ወደነበረው ሀህሮዝ ካምፕ ተመለሱ አላቸው። ከነአንን አላወርሳችሁም አላቸው። ወደ ተስፋዋ ምድር አትገቡም አላቸው። እስራኤሎች ወደ በረሀው ተመለሱ። በዚያም 40 አመት ቆዩ። (ዘ-ጸአት ምዕራፍ 13-14 ይመልከቱ) ይህን ጉዞ ሳስብ አሁን ካለው የአማራ ትግል ጋር ይመሳሰልብኛል። ከነአንን ልንወስድ ሲገባ እርስበርስ የአማራ ልጆች ስንባላ የያዘነውን ድል ልንነጠቅ ነው። እኛም ወደ ምድረበዳ እየተንከራተትን ነው። በዚሁ ከቀጠልን ደግሞ አሁን ያለው ትውልድ እንደስራኤሎች ይጠፋል የሚል ስጋት አለኝ። ምናልባትም የተስፋዋን ምድር የምንናፍቃትን ኢትዮጵያን ለማየት 40 አመት ወይም ከዚያ በላይ ሊፈጅብን ይችላል። እስራኤሎችን ፈጣሪያቸው ወደ ምድረ በዳው ለምን ተመለሱ አላቸው?ምክንያቱም ለፈጣሪያቸው አልታዘዙም። ከፈጣሪያቸው መና ይልቅ የግብጽን ጮማ ናፈቁ፣ አንድነት አጡ ፣ ፍቅር አጡ ተስፋ ቆረጡ። በመጨረሻም በረሀ በላቸው። ከመጀመሪያው ትውልድ ከ2 ሰው በስተቀር ከነንን ያያት የለም።የአማራም ትግል ዘ ጸአትን ይደግም ይሆን?የአማራ ትግል ከድጡ ወደ ማጡ እየሄደ ያለው አርቆ አስተዋይ በማጣቱ ነው፡፡ ጠላትና ወዳጁን መለየት የሚችልና በፖለቲካዊ ብልጠት መጓዝ የሚችል ደጋፊ በማጣቱ ነው፡፡ አብዛኛው ራሱን በራሱ የሚበላ እየሆነ ነው፡፡ ከገዳዩ ጠላት በላይ የራሱን ሰው ጠላት አድርጎ የሚታገል በመሆኑ ነው፡፡የአማራ ህዝብ ማን ነበርን ማን ነን? የአማራን ህዝብ 5 ሺ ዓመት የዘለቀ ታሪክ ለመጻፍ አቅሙ፣ በቂ እውቀቱም ኖሮኝ አይደለም። በወፍ በረር ግን ቁጭቴን ታሪክን አጣቅሼ ልግለጽ ብዬ ነው።ጀግናው የአማራ ሕዝብ ከዓለም ቀድሞ ሥልጣኔን ያስጀመረ፣ ለነገሮች ሁሉ ችግር ፈቺ መፍትሔ ማፍለቅ የሚችል፣ የመገልገያ ዕቃዎችን በራሱ ፈጠራ ገጣጥሞ የሚጠቀም፣ ትምህርት የሥልጣኔ መነሻ ነው የሚባለውን ፊደል ቀርጾ የጽሕፈት ሥልጣኔ የጀመረ ሕዝብ ነው፡፡የአማራ ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ፍልስፍና ያለው፣ ዛሬን ሳይሆን ነገን አርቆ የሚያስተውል፣ ጨዋነትንና ጀግንነትን፣ አብሮነትንና ለጋስነትን የተቸረ ሕዝብ ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ በእያንዳንዱ ስነ ልቦናዊ ጉዳይ ላይ ያለውን እምቅ ፍልስፍና ለማወቅ የሕዝቡን ስነ ቃል ማየት በቂ ምስክር ነው፡፡ ሌላ ጊዜ በዝርዝር እንመለስበታለን፡፡ይህ ሕዝብ ለምን አመድ ወለደ?‹‹ዘመናዊ›› የሚባለውን ትምህርት የተማርነው የአሁኖቹ የአማራ ልጆች ምን እንደነካን አይታወቅም! ከአማራ ሕዝብ ስነ ልቦና የራቅን ሆነናል፤ እጅግ ኋላ ቀርና ነገር ማሰብ የማንችል ሆነናል። በጣም ግልጽ የሆኑ ነገሮችን ማስረዳት ይሰለቻል፤ ይደክማል! ‹‹አማራ ከጎጥ አስተሳሰብ ወጥቶ አንድ ይሁን! ይደራጅ!›› ብዬ ለመጻፍ ሳስብ በአማራ ጠላቶች መሳቂያ የሚያደርገኝ ይመስለኛል! ትክክልም ናቸው! ጤነኛ በመሆን ብቻ ልናውቀው የሚገባውን ግልጽ ነገር መናገር አድካሚ ነው፡፡ አማራ ግን ለምን አመድ ወለደ?የአማራ ነገር ‹‹እሳት አመድ ወለደ!›› የሚለውን አባባል ያስታውሰኛል፡፡ በዲፕሎማሲ፣ በጦር አርበኝነት፣ በኪነ ጥበብ ከያኒነት…. በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፎች ኢትዮጵያን ያቀና ሕዝብ እንዴት እዚህ ላይ ወደቀ? እነዚያ ነበልባል የነበሩ ሰዎች እንዴት አመድ ወለዱ? እነ ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስን ያፈራ ምድር እንዴት እነ በለጠ ሞላን ሊቀበል ቻለ?ደፈር ብለን እንናገር ከተባለ አሁን አማራን እወክላለሁ የሚለው ኃይል ፈሪ እና ሆዳም ነው፡፡ ይሄ በግልጽ ሊነገረው ይገባል፡፡ ሥልጣን የሚያጓጓው ሆዳም ሆኗል፡፡ ለምሳሌ፡-ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚሰማው ነገር ጎጠኝነት ነው፡፡ ከዚህ በላይ አስቂኝ አላዋቂነት የለም፡፡ የእሱ ጎጥ ሰላም የሚሆነው አጠቃላይ አማራ ክብር ሲያገኝ መሆኑን አያውቅም፡፡ ጠላቶቹ የመጡበት ጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋ ወይም ወሎ ብለው ሳይሆን አማራ ብለው ነው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ቤቱን ያፈረሱበት ጎጃሜ ወይም ጎንደሬ፣ ሸዋዬ ወይም ወሎዬ ብለው አይደለም፤ አማራ ብለው ነው፡፡ ሰው እንዴት ይሄን መረዳት ይቸግረዋል?አብይ አህመድ ጎጃም እና ጎንደርን ለመከፋፈል ‹‹ጎንደርን ሳለማ ጎጃሞች ‹ምን ዋጋ አለው ጎንደር ሆነ! አሉኝ›› ብሏል፡፡ በእሱ ቤት ጎጃም እና ጎንደርን መከፋፈሉ ነው፡፡ ሰው እንዴት በዚህ ሰውዬ ይሸወዳል?አብይ አህመድ የትግራዩን ጦርነት ሊያስጀምር ሲል የአማራ ወዳጅ መስሎ ነበር፡፡ ሥልጣን በያዘ ገና በ3ኛ ወሩ ‹‹ትግሬ አማራን ለማጥፋት መሥራት የጀመረው አሁን አይደለም›› አለ፡፡ እዚህ ላይ ልብ መባል የነበረበት ነገር ትግሬ አማራን አጥቅቷል ወይስ አላጠቃም የሚለው አይደለም፡፡ ከአብይ አህመድ ንግግር ሊገርመን ይገባ የነበረው እንደዚህ ማለት ለምን ፈለገ የሚለውን ነው፡፡ በወያኔ ጊዜ አማራ ላይ ግፍ ይፈጸም ነበር የሚለውን የአማራ ምሁራን ቅሬታ ያስታውሳል፡፡ ስለዚህ በዚያን ወቅት ያንን ሲናገር አርቆ ማሰብ በማይችሉ አማሮች እንደሚወደድ ስለገባው ነው፡፡ አርቆ ማሰብ ማለት ትግሬ በአማራ ላይ ግፍ አልፈጸመም ማለት አይደለም፤ ዳሩ ግን ይህን ሊነግረኝ የሚገበው እንደ አብይ አህመድ አይነት መሃይም እና ጨካኝ አውሬ አይደለም፡፡ አብይ አህመድ ያኔ የአማራ ተቆርቋሪ መስሎ በኋላ ምን አደረገ? አፈ ሙዙን ወደ አማራ አዞሮ! አማራን መተታም እና ኋላቀር እያለ መሳደብ ጀመረ፡፡ ከዚህ ምን እንረዳለን?አንዱን የመውቀስ ሌላውን የማሞገስ አላማ አልያዝኹም። ነገር ግን ይህ የተራዘመ በአማራ መስተዳድር ላይ የታወጀ ጦርነት በይፋ 3 ኛ አመቱን ይዟል። ቀደም ብሎ ለ2 አመት ይፋዊ ያልሆ ጦርነት ነበር። በጥቅሉ 5 አመት ሆነው።ባለፉት አምስት አመታት በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ አማሮች ቁጥር 4 ሚሊዮን እንደሚጠጋ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) በአውሮፓውያኑ መስከረም 10 ቀን 2024ዓ ባወጣው ሪፖርት አሳውቋል። (አዲሱን ሪፖርት በዲሴምበር ይወጣል የከፋ እንጂ የተሻለ አዮንም) ።2024 ሪፖርቱን ራሳቸው የአማራ መስተዳድር ባለስልጣናት ጀብዱ የሰሩ ያክል በደስታ ተቀብለውታል።በክልሉ ላይ ለደረስ ሁለንተናዊጥፋት እና ኪሳራ የሚደስት አለ ብሎ ማመን እንደሰው ይከብዳል።የበአዴን /ብልጽግናዎች ግን ችግሩ ከጭንቅላታቸው ላይ ይሁን ጆሮአቸው ላይ አስደስቷቸዋል።የኦቻ ሪፖርት ሲቀጥል ፦ እንዲህ ይነበባል። በመስተዳድሩ በዘጠኝ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 43 ወረዳዎች እና 429 ቀበሌዎች ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በድርቅ ተጎምድተዋል። የፌዴራሉ አገዛዝ 1 ሚሊዮን ብቻ ነው ያመነው። 3 ሚሊዮን 556 ሺ 239 ተፈናቃዮች አሉ።፣ በድምሩ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች የዕለት ምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የመንግሥታቱ ድርጅት ገልጿል። 5552 ትምህርት ቤቶች የ1ኛ ደረጃና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከጥቅም ውጭ ተደርገዋል። 5772 ጤና ጣቢያዎች ክሊኒኮች ፣ ጤና ኬላዎች ሆን ተብሎ በአገዛዙ ወታደሮች ወድመዋል።ቀድሞ በ (USID undersevilance) የነበሩ የተለያየ በሽታ ተከታታዮች ድርጅቱም በመዘጋቱ እንዲሁም ጦርቱ ውድመት ባስከተለው የአገልግሎት እጦት እያለቁ ነው።የአብይ አይመድ ወታደር ልጃገዶችን እየደፈረ ነው። ኤች አይ ቪ ኤድስ በማስፋፋት ላይ ነው። ወሲብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀምም ከበሽታ ያመለጡት እንዲወልዱ እየተደረጉ ነው።ቀድሞ 11.6 ሚሊዮን ተማሪዎች በአመት ያስተምር የነበረው የአማራ ህዝብ አሁን 2.1 ብቻ ነው እያስተማረ ያለው። ለዚያው ይህ ቁጥር ውሸትን ግብሩ በአደረገው አገዛዝ ይፋ የተደረገ ነውና ተአማኒነቱ አጠያያቂ ነው። ይህ የቀጠለው ላለፉት አምስት አመታት ነው። ምን ያህል የትውልድ ክፍተት ሊፈጥር ሊፈጠር እንደሚች ይታሰብ። የ51 አመት በፊት ደርግ ስድሳ ምሁራንን ረሸነ። እነኝህ ምሁር ባለስልጣናት አብዛኞቹ ከልጅነታቸው ዘመን ጀምሮ ለሀገር መሪነት በመታጨታቸው የአብነት ከቅኔ እስከ ድጓ ያጠኑ፣ ቢያንስ ዳዊት የደገሙ ነበሩ። በአስኳላ ትምህርት በሕግ፣ በምጣኔ ኃብት፣ በፖለቲካዊ ሳይንስና የሕዝብ አስተዳድር፣ በካዴትነት ተደራራቢ ዘርፎችን የተማሩ ነበሩ። መንፈሳዊ ትምህርትን በሀገር ቤት፣ አለማዊ እውቀትን ደግሞ በውጭ ሀገራት የቀሰሙ ናቸው። ደርግ እነኝህን ረሽኖ ሀገሪቱን ለጋ ወታደሮች ተረከቡ። ይህም በተለይ በአማራ ላይ የትውልድ ክፍተትን ፈጠረ። ወያኔ በዘመኗ በአማራነታቸው ነጥላ 42 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ከሀገር አባረረች። ይህ የምሁራንን ፍልሰት አባብሶ አስቀጠለው። ታግሎ ከማሸነፍ ይልቅ ተሰድዶ መገላገል አማራጭ ኃሳብ ሆኖ ቀጠለ። ይህም ሌላኛው የትውል ክፍተት የታየበት ክስተት ነው። በትሉ ውስጥ ዛሬ እየታዩ ላሉ ችግሮች ሁሉ የትውድ ክፍተቶቹ የተጫወቱት ሚና ጉልህ ነው። ዛሬም የአብይ አሕመድ አገዛዝ በተራው አማራን ከትምህርት በማግለል ሌላ የትውልድ ክፍተት እየፈጠረ ይገኛል። የአማራ ህዝብ ከ20 አመት በኋላ ምናልባት አንዳች ምሁር ላይኖረው ይችላል። ዳንኤል ክብረት “ወደ ድንጋይ ዘመን ትመለሳላችሁ” ሲል የነገረን ይህንን ነው። ታዲያ አማሮች ይሄን መቅዘፍት በትክክል ተረድተነው ይሆን? ከተረዳነው ትግሉ ለምን ይረዝማል?

Discover more from wenchifEthiopia.com ወንጭፍ ኢትዮጵያ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading