ወቅታዊ መግለጫ!

https://wenchifethiopia.com/fotoplay20251018163748-mp4/ከአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ—
/
የአገዛዙ ጡት ቆረጣ የጄኖሳይድ ዓላማ እንዳለው ተጨባጭ ማሳያ ነው!!!
/
ጥቅምት 08፣ 2018 ዓ.ም።
/
የአማራ ህዝብ በፋሺስት ጣሊያን ለኳሽነት ማንነት ተኮር ጥቃት ከተከፈተበት 100 ዓመታት ለመቆጠር ትንሽ ዓመታት ብቻ ናቸው የቀሩት። በዚህ አንድ ክፍለ-ዘመን ባስቆጠረ የማጥላላት፣ የመፈረጅ፣ የማግለል፣ የማፈናቀል እና የመግደል ጥቃት ለአእምሮ የሚሰቀጥጡ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ተፈፅመዋል።በፋሺስት ጣሊያን የተፈፀሙት ሳይካተቱ፣ ባለፉት 50 ዓመታት አማራ በማንነቱ እየተለየ ከተፈፀሙበት የጅምላ ጥቃቶች መካከል ንፁሃን መጋዝን ውስጥ ተቆልፎባቸው እሳት ተለቆባቸዋል፣ እርጉዞች በስለት ተቀደው ፅንሳቸው እንዲወጣ ተደርጓል፣ ጡት የሚጠቡ ህፃናት ተገድለዋል፣ ሰዎች እንደ በግ ከአንገታቸው ታርደዋል፣እንደ ታደነ አውሬ ተዘቅዝቀው ከተሰቀሉ አስከሬኖች ጎን ሰዎች ፎቶግራፍ ተነስተዋል፣ “አማራ መሬታችን ላይ አይቀበርም” ተብሎ ቀብር እንኳን ተከልክሏል። ይህን ሁሉ የምናስታውሰው ለበቀል ግብአት እንዲሆን ሳይሆን፣ ስለዘረኝነት አደጋ ማስተማሪያ እንዲሆን ነው። ከታሪክ የማይማር የታሪክን ስህተት እየደጋገመ ይኖራልና።ይህ ሁሉ የዘመናችን ግፍ የተፈፀመው ከ100 ዓመታት በፊት በታሪክ ደረሰብን ለሚባል በደል መሆኑ የትራጄዲውን ደረጃ በእጅጉ ከፍ የሚያደርግ ነው። የጥላቻ ፖለቲካ ነጋዴዎች ከመቶ ዓመታት በፊት ተፈፀመ ለሚሉት ምናባዊ በደል “አማራን ላለፉት 50 ዓመታት እያስከፈልነው ነው” ከሚሉት “የደም ካሳ” ባሻገር፣ የምናባዊ በደላቸው ተምሳሌት ነው የሚሉትን አኖሌ ሐውልት አቁመውለታል።ይህ ሐውልት ተፈፀመ ለሚባለው ምናባዊ ጡት ቆረጣ ተጨባጭ ማስረጃ እንዳልተገኘለት የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋገጡት በመሆኑ መገንባት ያልነበረበት ቢሆንም፣ ወይም በስህተት ቢገነባ እንኳን መፍረስ የነበረበት ቢሆንም፣ ዓላማው መጀመሪያውንም ቢሆን ታሪክ ሳይሆን፣ አማራን ዒላማ ያደረገ እና ጄኖሳይድ መቋጫው የሆነ ብቀላን ለአዲሱ ትውልድ ማስተማር በመሆኑ፣ አስካሁን ድረስ ቆሞ ይገኛል። እንደታለመለትም፣ በአማራ ክልል አራቱም ጠቅላይ ግዛቶች ለተፈፀሙ አረመኔያዊ ወንጀሎች ፖለቲካዊ ምንጭ—political inspiration—ሆኗል።በጎጃም እና በወሎ ጠቅላይ ግዛቶች በእነ ፋኒት በዓለም ዋሴ እና ፋኒት ትዕግስት ወዳጆ፣ በሸዋ እና ጎነደር እነ ፋኒት ቃልኪዳን ለምናባዊው ጡት ቆረጣ ምላሽ እንዲሆን ተደርጎ የተፈፀመባቸው ጡት ቆረጣ በአማራ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በመላ ኢትዮጰያዊያን እና የሰው ልጆች ላይ ሁሉ የተፈፀመ አረመኔያዊ ወንጀል ነው። ድርጊቱ አገዛዙ የጄኖሳይድ ዓላማ እንዳለውም ግልፅ ማሳያ ነው።ይህ አረመኔያዊ ድርጊት በተጨባጭ ስለመፈፀሙ በምስል ቀርቦም እያለ፣ በአገዛዙ በኩል ምንም ትንፍሽ አለመባሉ “ነገሩን ላለማባባስ” በሚል ነው ብሎ የሚያስብ ካለ በእጅጉ ተሳስቷል። በጦር ሜዳ እየተሸነፈ የተቸገረው አገዛዙ፣ በአንድ በኩል ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጋጨትና ለመከፋፈል፣ በሌላ በኩል፣ ፍርሃትን እንደ ሥነ ልቦና መሣሪያ ለመጠቀም እየሞከረ ስለመሆኑ የሚከተሉትን እውነታዎች በማየት መረዳት ይቻላል:-1–ድርጊቱ በተለያዩ ቦታዎች በተመሳሳይ መንገድ መፈፀሙ በእቅድ መፈፀሙን በተጨባጭ ያረጋግጣል፣2—እቅድ ካለ የሚያስፈፅም አካል እንደሚኖር በግልፅ ይታወቃል፣3–ድርጊቱ በፋኖ አባላት ላይ ብቻ የተፈፀመ በመሆኑ፣ ፈፀሚው አካል መንግሥታዊ ኃይል መሆኑን ያሳያል፣4–በድርጊቱ በህብረተሰቡ ውስጥ ሊቀሰቀስ የተፈለገ የበቀል ስሜት እንዳለ ከአኖሌ ሐውልት ተምሳሌትነት መረዳት ይቻላል፣5–በድርጊቱ በፍርሃት ተሸማቆ ስሜቱ እንዲሰበር የተፈለገ ማህበረሰብ እንዳለም በቀላሉ መረዳት አይከብድም።አገዛዞች በውድቀታቸው ዋዜማ በሚያደርጉት መፈራገጥ ብዙ ወንጀሎችን እንደሚፈፅሙ በታሪክ የተረጋገጠ ቢሆንም፣ ይህኛው ድርጊት ግን አዲስ ዝቅታ —-low point—መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም።የአማራ ህዝብም ሆነ ፋኖ አገዛዙ ባዘጋጀው ወጥመድ ውስጥ ገብተው እና በበቀል ስሜት ተነሳስተው የሚፈፅሙት የታሪክ ወንጀል፣ ስህተት እና ጠባሳ ፈፅሞ የለም የምንለው በልበ ሙልነት ነው። የኢትዮጰያ ታሪክ የአማራ ህዝብ የሰከነ ስለመሆኑ ምስክር ነው። ከአማራ አብራክ የወጣው ፋኖም፣ ገና 3 ዓመታት እንኳን ያልሞላው ቢሆንም፣ ከእድሜው በላይ የሰከነ መሆኑን በየዕለቱ እያስመሰከረ ይገኛል።ጡታቸው የተቆረጡትን ሰመዓቶቻችን በሚመለከት እንደአማራም እንደፋኖም ፍትህ እንጠይቃለን፣ ለፍትህ እንታገላለን፣ ፍትህንም እናስከብራለን። በዚህ ወንጀል ተሳታፊ የሆኑ ሁሉ በህግ ይጠየቃሉ፣ ይህን ሳናረጋግጥ ትግላችን አይቆምም።ለዚህ የተቀደሰ ተግባር መላ ኢትዮጰያዊያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት እና የውጭ መንግሥታት ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪ እናቀርባለን።ክብር እና ሞገስ ጡታቸው ለተቆረጠባቸው ሰማዕቶቻችን!!!ድል ለአፋህድ እና የአማራ ፋኖ ሁሉ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለኢትዮጰያ ህዝብ!!!
/
ጥቅምት 08፣ 2018 ዓ.ም።

Discover more from wenchifEthiopia.com ወንጭፍ ኢትዮጵያ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading