ቴዲ አፍሮ ቢታሰር ምን ይመጣል?

ቴዲ አፍሮ ቢታሰር ምን ይመጣል?
…………………………………………………
ሞገድ እጅጉ
ጀግንነትን የማያውቀው እና በማታለል ሥልጣን የያዘው ወንጌላዊው የአብይ አህመድ መንግሥት አሸንፎ እንኳን ይፈራል። አሸንፏል ሲባል ታግሎ ወይም በምርጫ ሳይሆን ይሉኝታ ቢስ እና ሐፍረተ ቢስ ሆኖ ሥልጣን ላይ በመቀጠል ማለት ነው። ተበደልኩ ብሎ የጠየቀው ሕዝብ ስለሌለ ፈሪው የአብይ አህመድ አገዛዝ ሥልጣን ላይ ይገኛል።
ይህ ፈሪ አገዛዝ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁንን(ቴዲ አፍሮ) በአንድ ጊዜ ለማሰር የፈራ ይመስላል። የሕዝብ ተቃውሞ ይነሳል ብሎ የጠረጠረ ይመስላል። ለዚህም ነው ቀስ ብሎ የማላመድ ሥራ እየሰራ ያለው።
መጀመሪያ በአርቲስቱ ዙሪያ ያሉ የቅርብ ሰዎቹን እና የሥራ ኃላፊዎችን ማሰር ጀመረ። በዚህ እያላመደ ዛሬ ደግሞ የአርቲስቱን የመስሪያ ስቲዲዮ እንደ ሽፍታ ገብቶ ዘረፈ። ዘረፋውን የፈጸመው የታጠቁ ኃይሎችን በማሰማራት እንደሆነ የጀርመን ድምጽ(ዶቼቬለ) ዘግቧል። እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች ሲፈጸሙ የቴዲ አፍሮ አድናቂዎችም ሆኑ ሌላው ሕዝብ “አይ! ይሄ መንግሥት!” ከማለት ያለፈ ምንም አላደረጉም፤ ምንም ሊያደርጉም አይችሉም።
አንዳንድ የዋህ ሰዎች ቴዲ አፍሮ ቢታሰር አድናቂዎቹ የተቃውሞ ሰልፍ ይወጣሉ ብለው ያስባሉ። ይህ የአዲስ አበባን ነዋሪ ስነ ልቦና ካለመረዳት እና ካለማወቅ የመጣ የዋህነት ነው፤ ወይም ቢሆን ብሎ ከመመኘት የሚመጣ ነው። ዳሩ ግን ምኞት እና ተጠይቃዊ ሀቅ ደግሞ ይለያያል፤ መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ የሚያሳየው መንግሥት ቴዲ አፍሮን እንኳንስ ማሰር ቢገድለው ምንም እንደማይመጣ ነው። ይህን እውነታ መረዳት የማይችል ካለ ለማስረዳት አድካሚና አሰልቺ ነው።
ከላዩ ላይ ቤቱ ሲፈርስበት የፈጣሪ ቁጣ ነው ብሎ ዝም ያለ ነዋሪ ቴዲ አፍሮ ታሰረ ብሎ ለተቃውሞ አይነሳም። ቤትህ ሊፈርስ ነው ውጣ ተብሎ ሲነገረው ከሱቅ ገመድ ገዝቶ ራሱን የሚያጠፋ ስነ ልቦና ያለው ሕዝብ በቴዲ አፍሮ መታሰር ትንፍሽ አይልም። አሳቢ ቢሆን ኖሮ መሞቱ ካልቀረ አንዱን አፍራሽ አናቱን አፍርሶ መሞት ይሻለኛል ብሎ ያስብ ነበር።
አገዛዙ ቴዲ አፍሮን በአንድ ጊዜ ማሰር ምናልባት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አጀንዳ እንዳይሆንበት የፈለገ ይመስላል። ስለዚህ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እያለማመደ ነው። ማሰሩ ተጠባቂ እንደሚሆን ማሳየት ነው። ከዚያ በኋላ ምንም ቢያደርገው ተጠባቂ እና ተገማች ይሆናል ማለት ነው።
አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ(በተለይም አዲስ አበቤ) ለውጥ የሚመኝ ከሆነም ለውጡ በሌላ አካል እንደመጣ ይመኛል እንጂ ራሱ ተሳታፊ አይሆንም። የከተማ ልጅ ነኝ ቢልም የሰለጠነውን የከተማ ሰላማዊ ተቃውሞ ለማድረግ ይፈራል። ከፍርሃቱ በተጨማሪ ደግሞ አዲስ አበቤውም በብሔር ስነ ልቦና ማሰብ ጀምሯል። አሁን ያለው አገዛዝ ይሉኝታ ቢስ እና ሀፍረተ ቢስ ስለሆነ አጥብቆ ይፈራል።
የልጆቹ አምላክ አያድርግበትና አገዛዙ ቴዲ አፍሮን ቢገድለው፤ ጨርቃቸውን ጥለው የሚያብዱለት የቴዲ አድናቂዎች እስከ ሳምንት ከቤት እንኳን ላይወጡ ይችላሉ። የሚያሳዝነው ነገር የሁሉም ፍርሃት ግጭት ይነሳል የሚል ነው፤ ሁሉም እንደዚህ ብሎ እያሰበ ከቤት አይወጣም። ስለዚህ ግጭቱን የሚያስነሳው አይኖርም። ግጭት ብለው የሚፈሩት በሰላማዊ መንገድ መጠየቅን ነው። እነዚህ ፈሪዎች ግን አዲስ አበበባ ድብልቅልቋ ወጥቶ ለውጥ እንደመጣ ይመኛሉ። ነዋሪዎች እንዲህ እየተመኙ ምን አይነት አስማታዊ ኃይል ለውጡን እንደሚያመጣው አይታወቅም!
የቴዲ አፍሮ አድናቂዎችም ሆኑ ሌላው ለውጥ የሚመኝ ሕዝብ ማወቅ ያለበት ነገር ለውጥ በራሳችሁ እንጂ በሌላ ተዓምር አይመጣም!

AFPO addressing the current situation!

AFPO urgent press release.
/
Call for clarification by AU and IGAD regarding the fraudulent peace agreement between AFPO and Ethiopia’s genocidal regime.
/
—- December 5, 2025.
/
AFPO deeply regrets AU and IGAD statements regarding the fraudulent peace agreement between AFPO and a shadow of the Amhara regional government, which dissolved by popular revolution two years ago and has been replaced by Federal military rule.

Both AU and IGAD know very well that no negotiations had ever taken place between AFPO and Ethiopia’s genocidal regime. As recently as three to four weeks ago, AFPO’s chairperson, Eskinder Nega, had told the deputy chairperson of the AU, H.E. Selma Malika Haddadi, that no negotiations had ever taken place between AFPO and the regime, and that there was no intention to do so in the future.

H.E. Selma Malika Haddadi, a new appointee to her position, promised to explore the issue further with her organization and get back to us. We have yet to hear from her.

In lieu of IGAD’s obvious conflict of interest, whose leader, Gebeyehu Werkeneh, is a proud loyalist of Ethiopia’s ruling party, no two way contact has ever taken place between us. What contact we had were all in multilateral settings.

Ethiopia’s habitually lying genocidal regime has claimed that both the AU and IGAD had mediated the so-called peace negotiation between AFPO and itself. And while the statements issued by the two organizations indeed stress that they had only attended the so-called signing ceremony, which was between an individual with no following and a non-existent regional government, we urge H.E. Selma Malika Haddadi to give a full public account of the AU’s engagement with AFPO.Despite the conflict of interest, IGAD too should do the same.

This fraudulent peace agreement has diminished the possibility of peaceful resolution to the war even more than ever. And while this is in confluence with the delusional plans of the regime, the good name of an esteemed body as that of the AU should not be dragged into it.

We urge the AU and H.E. Selma Malika Haddadi in particular to tell the world the full truth. While lies profit war, truth profits peace.

In truth we trust !!!

Amhara Fano People’s Organization.
December 5, 2025.

አፍሀድ አስቸኳይ መግለጫ አወጣ

አፋህድ አስቸኳይ መግለጫ

—ህዳር 25፣ 2018 ዓ.ም!!!
/
አፋህድ በጦርነት እያሸነፈው ካለው አገዛዝ ጋር የፈረመው ስምምነት የለም!!!
/
በፋኖ ብርቱ ትግል እየተመታ ለመውደቅ እየተንገዳገደ መያዣውና መጨበጫው የጠፋው የኦህዴድ/ብልፅግና አገዛዝ፣ ከፈረሰ ሁለት ዓመታትን ካስቆጠረው የአማራ ክልል መንግሥት የሙት መንፈስ ጋር የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የ”ሰላም ስምምነት” አደረገ ብሎ ዛሬ ረፋዱን ያወጣው መግለጫ ፍፁም ሐሰት ነው።

አፋህድ ከኦህዴድ/ብልፅግናም ሆነ ከአማራ ክልል መንግሥት ተብዬው የሙት መንፈስ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተገናኝተን ድርድር አድርጎ አያውቅም። ከአገዛዙ ጋር የምንገናኘው በጦር ሜዳ ላይ ብቻ ነው።

በምናባዊ ዓለም ተደረገ በተባለው ድርድር ተገኝተዋል የተባሉት የአፍሪቃ ህብረት እና ኢጋድ በቀጣይ ቀናት ይፋዊ መግለጫ እንዲሰጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናቀርባለን።

በአፋህድ በኩል ስምምነት ፈረመ የተባለው ማስረሻ ሰጤ፣ ከአገዛዙ ጋር ተልዕኮ ተቀብሎ ሲንቀሳቀስ ተደርሶበት ከአመራርነት እና አባልነት የታገደ እና የተባረረ መሆኑን በዚህ ሳምንት ባወጣነው መግለጫ መግለፃችን ይታወሳል። ከአገዛዙ ጋር ሲቀላቀልም፣ ለስራ ተብሎ የተላከለት በርካታ ያልተወራረደ የህዝብ ገንዘብ በእጁ እንደሚገኝ እና “የሰላም ስምምነቱን” ለዘረፋ ሽፋን ለማድረግ ከአገዛዙ ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

አገዛዙ ሰሞኑን በተለያዩ በበሬ ወለድ ዜናዎች የሚፈራገጠው የፋኖ አንድነት ለማደናቀፍ ብሎ መሆኑን ህዝብ ተገንዝቦ፣ በቀጣይነት የምናወጣቸውን መግለጫዎች እንዲጠባበቅ እናሳስባለን።

ክብር እና ሞገስ ለሰማዕታት!!!

ድል ለአፋህድ እና የአማራ ፋኖ ሁሉ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
/
ህዳር 25፣ 2018 ዓ.ም።

አፋህድ በመተከል በአማሮች ላይ ጂኖሳይድ መፈጸሙን አወገዘ።

የአፋህድ የህዳር 15፣ 2018 ዓ.ም አስቸኳይ መግለጫ!!!
/
በመተከል በአማራ ላይ የተፈፀመው የጄኖሳይድ ጥቃትን በጥብቅ እናወግዛለን፣ ትግላችንን በማጠናከር ተግባራዊ ምላሽ እንሰጣለን!!!
/
ህዳር 15፣2018 ዓ.ም
/
አማራን ለመበቀል እና ለማዳከም ተብሎ ከጎጃም ጠቅላይ ግዛት ላይ ያለ ህዝብ ፍቃድ እና ይሁንታ በኃይል ተቦጭቆ በተወሰደው መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ ከዚህ በፊት አማራዎች በጅምላ ተጨፍጭፈው በአንድ ጉድጓድ ውስጥ በተቀበሩበት “በኩጂ” ቀበሌ ህዳር 13፣ 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት በአማራ ላይ በተፈፀመ ብሄር ተኮር የጅምላ ጥቃት ከ40 በላይ ህፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋዊያን እና ሰላማዊ ገበሬዎች በታጣቂዎች በጅምላ የተጨፈጨፉ ሲሆን፣ ለግዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ደግሞ ቆስለው በህይወት እና ሞት መካከል እየዋዠቁ በመሆኑ፣ የሟቾች ቁጥር በቀጣይ ቀናት ይጨምራል ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡

በስልጣን ቢጣሉም በዓላማ እና ግብ አንድ በሆኑት ኦህዴድ/ብልፅግና እና ሽኔ የተቀነባበረው ይህ ጄኖሳዳዊ ጭፍጨፋ ዒላማ ያደረገው በጠላትነት የፈረጁትን አማራን ቢሆንም፣ በሩዋንዳ ጄኖሳይድ ከተፈፀመበት ቱትሲ ጋር የተገኙ የሁቱ ብሄር አባላት አብረው እንደተጨፈጨፉት ሁሉ፣ አሁንም ከአማራ ጋር አብረው የተገኙ የሺናሻ እና ጉምዝ ማህበረሰብ አባላትም ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፣ የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል። ይህም፣ በአማራ ላይ የተለኮሰው የጄኖሳይድ ጦርነት መላ ኢትዮጰያዊያንን የሚበላ እሳት ስለመሆኑ ተጨባጭ ማሳያ ነው።

የአማራ ህዝብ ከመቼውም ግዜ በላይ ራሱን ከጅምላ ጥቃት ለመከላከል የጀመረውን ትግል እንዲያጠናክር ይህ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ የማንቂያ ደወል ሊሆነው ይገባል። የጄኖሳይድ አደጋው በትግላችን ያመከነው ያለፈ ችግር አይደለም። ራሳችንን ለመከላከል እየታገልን ባለንበት የአሁኑ ግዜ በላያችን ላይ ያጠላ አደጋ ቢሆንም፣ በዚያ ብቻ የተገደበም አይደለም። እንዲያውም ከሁሉም በላይ፣ ነገ እና ተነጎዲያ ከፍተኛ ጥፋት ሊያደርስ የሚችል በይደር የተቀመጠ አደጋ መሆኑ በተለይ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እየተደረጉ ከሚገኙት ወታደራዊ ዝግጅቶች አኳያ ቁልጭ ብሎ የሚታይ ታሪካዊ ፈተና ነው።

በዚህ አውድ የአማራ ህዝብ የመጀመሪያ መሥመር መከላከያው የፋኖ ትግል ነው። እስካሁን ባለው ሂደት፣ ይህን ትግል የሰው ኃይል በማዋጣትም ሆነ በፋይናንስ በመደገፍ በሁለቱም ትከሻው ተሸክሞ የሚገኘው ደሃው አርሶ አደር ነው። ምንም እንኳን ይህ የህብረተሰባችን ክፍል “ሰለቸኝ፣ ደከመኝ” ብሎ የተማረረ ባይሆንም፣ የከተማ ነዋሪዎች፣ ነጋዴው፣ ሙህራን፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የአገዛዙ ሠራዊት አባላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና ሌሎችም በተደገሰው የጅምላ ጭፍጨፋ በመጀመሪያ ረድፍነት የተቀመጣችኹ እናንተ መሆናችሁን ተረድታችኹ የህልውና ትግሉን የምትቀላቀሉበት ወይም ካላችኹበት ሆናችኹ የምታግዙበትን ሁኔታ እንድታመቻቹ እንማፀናችኋለን።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለረዥም ግዜ የምናቀርባቸውን ተማፅዕኖዎች እና ጥሪዎች ምላሽ የነፈገን መሆኑ የማይጠፋን ቢሆንም፣ ተሰማንም አልተሰማንም የጥቃት ሰለባ ለሆኑ ንፁሃን ድምፅ የመሆን ግዴታ እንዳለብን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ይህን ድርጊትም ሆነ ከዚህ በፊት የተፈፀሙትን አሰቃቂ የጅምላ ወንጀሎች የሚመረምር ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ ምርመራ እንዲያደርግ እና ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን።

ክብር እና ሞገስ ለሰማዕታት!!!

ድል ለአፋህድ እና የአማራ ፋኖ ሁሉ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለኢትዮጰያ ህዝብ!!!
/
ህዳር 15፣ 2018 ዓ.ም።

አፋህድ የመንግስት ጂኖሳይዳዊ ወንጀሎች አጋለጠ

የአፋህድ ወቅታዊ መግለጫ!!!
/
በአማራ ላይ በአገዛዙ ወታደሮች የሚፈፀሙ የጾታ ጥቃቶች የጄኖሳይድ ወንጀሎች ስለሆኑ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት(UN) አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል!!!
/
ህዳር 12፣ 2018 ዓ.ም።
/
በአማራ ክልል በሴቶች እና በህጻናት ላይ የአገዛዙ ጦር አባላት በሰፊው የሚፈፅሙት የጾታ ጥቃቶች ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሱ በመሄድ ላይ ናቸው። በታሪክ ጄኖሳይድ በተፈፀመባቸው ሀገራት በውል እንደታየው፣ የፆታ ጥቃት የጄኖሳይደሮች አንደኛው ተመራጭ መሣሪያ ነው። የጥቃት ሰለባዎቹ እድሜ ከ 8 ዓመት አንስቶ እስከ 70 ዎቹ ድረስ መሆኑ፣ ዓላማው ከወሲባዊ አርካታ ይልቅ ህዝብን በሥነ ልቦና ሰብሮ ለተጨማሪ እልቂት እንዲመች ማድረግ መሆኑን በተጨባጭ ያሳያል።

አማራ ከመንግሥታዊ የጅምላ ጭፍጨፋ ራሱን ለመከላከል እንደ ህዝብ ወደ ትጥቅ ትግል ከገባበት 2015 ዓ.ም አንስቶ፣ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች የተፈፀመባቸው ህፃናት እና ሴቶች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው።

እነዚህ ጥቃቶች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የተፈፀሙት በገጠራማ አካባቢዎች ወይም አንሰተኛ ከተሞች በመሆኑ፣ የህክምና ተቋማት በአቅራቢያ ስለሌሉ አብዛኞቹ ወንጀሎች ተሸፋፍነው ይገኛሉ። ሆኖም፣ አመቺ ሁኔታ ከተፈጠረ ብዙዎቹ ተሸፋፍነው እንደማይቀሩ በጉዳዩ ዙሪያ ጥናት ያደረጉ አካላት አረጋግጠዋል።

ስለዚህም፣ እንዲህ ዓይነቱ አፀያፊ ወንጀል በጅምላ ሲፈፀም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዝምታ ፈፅሞ ሊያልፈው የሚችልበት አግባብ የሌለ በመሆኑ፣ በተባበሩት መንግሥታት (United Nations) የበላይነት ገለልተኛ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ የሚከተሉት እርምጃዎች እንዲወሰዱ እንጠይቃለን :-

1—በአማራ ክልል ባለው ጦርነት የተፈፀሙ የጾታ ጥቃቶችን የሚመረምር የባለሙያዎች ቡድን በተባበሩት መንግሥታት አስተባባሪነት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተውጣጥቶ እንዲቋቋም፣

2— በአማራ ክልል ያሉ ተፋላሚ ወገኖች ለመርማሪ ቡድኑ ያለ ምንም ቅድመና ሁኔታ ቅድሚያ እውቅና እንዲሰጡ፣ በሚቆጣጠሯቸው መሬቶች መርማሪ ቡድኑ በነፃነት እንዲንቀሳቀስ እንዲፈቅዱ፣ ለመርማሪ ቡድኑ የደህንነት ዋስትና እንዲሰጡና ሙሉ ትብብር እንዲያደርጉ፣

3— መርማሪ ቡድኑ በሚያወጣው የመጨረሻ ሪፖርት መሠረት ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ፣

4— በተባበሩት መንግስታት አስተባባሪነት ለተጎጂዎች ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና ክትትል ከነፃ መድኃኒት ጋር እንዲሰጥ እና የስነ-ልቦና ድጋፍ እንዲደረግላቸው እንጠይቃለን።

የጄኖሳይደሮች የተቀነባበረ ሰለባ የሆኑ የአማራ ህፃናት እና ሴቶች ድምፅ ሊሰማ ይገባል። በይበልጥም ፍትህ ሊያገኙ ይገባል። የተባበሩት መንግሥታት በአፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባዋል። የዘገየ ፍትህ እንደ ተነፈገ ፍትህ ይቆጠራል።

ክብር እና ሞገስ ጥቃት ለደረሰባቸው የአማራ ህፃናት እና ሴቶች!!!

ድል ለአፋህድ እና የአማራ ፋኖ ሁሉ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
/
ህዳር 12፣ 2018 ዓ.ም።