Category: Article

  • የብልጽግና ፍርድ ቤት በህሊና ስረኞች ላይ በአካል የማይቀርብ ሀስተኛ ምስክሮች አዘጋጀ!

    በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ 16 ሰዎች ላይ አንድ ሰው ሕዳር 12 ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ ሊመሰክር ነው ፤ የተከሳሾች ጠበቆችም የምስክር ሂደቱን በመቃወም ጉዳዩን በይግባኝ እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ወስደውት ነበር።

    (አውሎግሶን አንድነት- Awulogson Andinet ፣ ጥቅምት 18/2018 ፣ አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ)

    በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው መዝገብ 16 ሰዎች ላይ አንድ ሰው ሕዳር 12/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ እንዲመሰክር በሚል ቀጠሮ ተይዞለታል።

    አማራነታችን እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ለአፈና ፣ ለእገታ ፣ ለስወራ በመጨረሻም ለእስር ተዳርገናል የሚሉት የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞቹ ምንም እንኳ የፈጠራ እና የማንነት ሽልማት ቢሆንምገዘ ከ15 ዓመት እስከ እድሜ እና ሞት የሚያስቀጣ የሽብር ክስ የተመሰረተብን በመሆኑ መመስከር ያለበት ከመጋረጃ በስተጀርባ ተደብቆ ሳይሆን በግልጽ ችሎት ሊሆን ይገባል ሲሉ ሂደቱን ተቃውመውታል።

    “ይታያል በሩቁ” የሚል የፈጠራ ስም የተሰጠው ይህ የዐቃቤ ሕግ ምስክር በመጀመሪያውና ተሻሻለ በተባለው የሽብር ክስ ስሙ አልተካተተም ፤ ዐቃቤ ሕግ አሉኝ ካላቸው 21 ምስክሮች መካከልም 15 የሚሆኑ የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችንና አባላትን ካስመሰከረና ሂደቱን ከገመገመ በኋላ ክፍተቱን ለመሙላት ሲል አሰልጥኖ ያመጣው በመሆኑ ከመጋረጃ በስተ ጀርባ ተደብቆ ሊመሰክር አይገባም በማለት ተከራክረው ነበር።

    ሌሎች ለከሳሽ የወገኑ ያሏቸውን ተደጋጋሚ የችሎት ክፍተቶችን በማካተትም ፍ/ቤቱ የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ የፖለቲካ ፍላጎት ማስፈፀሚያ እየሆነ ነው ፤ በመሆኑም ይህ የፍትህ ሂደቱን የሚያዛባ አካሄድ እስካልታረመ ድረስ የሂደቱ አካል ሆነን ለመቀጠል ይቸግረናል በማለት ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ ማውጣታቸውም ይታወሳል።

    የተከሳሾች ጠበቆችም ምንም እንኳ በመጨረሻ ውሳኔውን ለማስቀልበስ ባይችሉም ቢያንስ ለታሪክ ይሆናል በሚል የተደብቆ ምስክር ሂደትን በመቃወም እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ሄደው መድከማቸው ግልጽ ታውቋል።

    ጠቅላይም ሆነ ሰበር ሰሚ ችሎት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት እንደወሰነው ለደህንነቱ ሲባል በመጋረጃ ተደብቆ ይመስክርባቸው በማለት በመወሰናቸው ነው ለሕዳር 12/2018 ቀጠሮ የተያዘው።

    ይህ ቀጠሮ የተሰጠውም ተከሳሾች ጥቅምት 18/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት መቅረባቸውን ተከትሎ ነው።

    በእለቱም የቂሊንጦ ማ/ቤት ኃላፊዎች በተለይም በፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ፣ ቤተሰቦችና ጠበቆች ላይ በፍተሻ ስም ማንነትን እና ሰብአዊ ክብርን እየጣሱ ነው ፤ በማንነት እየተሳደቡ ነው ፣ የተከሳሾችንና የጠበቆችን ሰነድ እየነጠቁ ነው ፣ ከጠበቆችና ከቤተሰቦች ጋር ግንኙነት እየከለከሉ ነው ፣ እስረኛን ከመደብደብ እና ከማንገላታት አልፈው ሕክምና ጭምር እየከለከሉ ነው በሚል ለቀረበ ክስ የግቢው ጥበቃ እና ደህንነት ኃላፊ መሆናቸውን የገለጹ ኢ/ር ድሪባ ሰንበታ ቀርበው አብዛኛውን ክስ በማስተባበል ምላሽ ሰጥተዋል።

    ተከሳሾች እና ጠበቆችም እድሉ ስለተሰጣቸው ደርሷል ያሉትን ግፍ እና በደል ሁሉ በዝርዝር አስረድተዋል።

    ችሎቱም ጉዳዩን መርምሮ ተገቢ ነው ያለውን ትዕዛዝ ለመስጠት በሚል ለጥቅምት 26/2018 ቀጠሮ ስለመያዙ ለአውሎግሶን አንድነት የደረሰው መረጃ አመልክቷል ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ የምናጋራ ይሆናል።

  • AFPO Manifesto Press release, October24/2025

    AFPO Manifesto Press release, October 24, 2025.
    /

    T

    he way forward for Ethiopia—Constitutional remedy for a constitutional crisis.
    /
    The cliché in Ethiopian politics which has dogged the entirety of all opposition that has risen against Ethiopia’s three decade ruling party, is the alleged absence of a viable blueprint for a possible post-regime scenario.

    As a rural based armed resistance, this charge has particularly resonated against the Fano movement. It was as if though the default thinking was that a rural based movement, while a legitimate expression of a people’s grievances, was structurally unfit to reflect on broader political issues.

    But history says otherwise. While rural based resistance movements had indeed mostly sprang up as an antidote to oppression , they had also amply demonstrated that they are capable of metamorphosing into mature organizations which go on to craft enduring constitutional orders in their countries.

    Such has been the trajectory of Fano for the past two years. And nothing encapsulates this reality than the finalization and ratification of AFPO’s manifesto by the Executive Committee, the highest decision making body of our organization.

    At the root of Ethiopia’s crisis, in which genocide has become the focal-point of conflict between the state and its citizens, lies a constitution uniquely empowered to permanently politicise hate infused ethnic politics.

    At the heart of AFPO’s blueprint for a new era in Ethiopia is a constitutional decoupling between ethnicity and state, similar in many ways to the separation between state and religion.

    Some of the highlights from the manifesto include the following pointers:-

    1— Ethiopia’s territorial integrity, sovereignty, and national interests must be protected
    without compromise.

    2— All religious and cultural identities and values of all Ethiopian communities must be preserved as precious heritages of humanity.

    3— Ethiopia must have a robust security structure to protect citizens from any internal or external aggression and ensure national and regional peace.

    4— The country’s administrative structure should follow a progressive federal system.

    5— When structuring federal administrative territories, considerations should include expediency for development and administration, population distribution, popular sentiment and will, historical and psychological ties and geographical proximity, all to be determined through inclusive discussions and mandates.

    6—-Land ownership should be structured under four
    categories: individual, government, religious institutions, and community. Laws will be amended to allow for the sale, exchange, banking, and inheritance of rural and urban private land.

    While there are more pointers we could cite regarding economic and social affairs, we invite all to read the manifesto in its entirety at the following link:

    Link to the manifesto-

    https-://thevoiceoffano.com/storage/2025/10/AFPO-Manifesto_Bilingual_20October2025.pdf

    Glory to all martyrs!!!

    — Victory to AFPO and all Amhara Fano forces!!!

    —Victory to the Amhara people !!!

    Victory to the Ethiopian people !!!
    /
    October 24, 2025.

    Click to access AFPO-Manifesto_Bilingual_20October2025.pdf

  • አፋህድ ማኒፌስቶውን ይፋ አደረገ!

    አፋሕድ የጥቅምት 12፣ 2018 ዓ.ም
    ወቅታዊ መግለጫ— አፋሕድ የፋኖን የመጀመሪያ የተሟላ ፍኖተ-መርህ (ማኒፌስቶ) ይፋ አድርጓል !!!
    /
    -ጥቅምት — 12፣ 2018 ዓ.ም።
    /
    ከብሶት ትግል ወደ መርህ ትግል የሚያሸጋግረን የአማራ ተጋድሎ የወደፊት ተስፋ የሆነው ይህ ፍኖተ-መርህ ተጠናቋል።

    የፋኖ እንቅስቃሴ በምስራቅ አፍሪካ ካሉት ግዙፍ ሃይሎች አንዱ ወደ መሆን ተሸጋግሯል። በወታደራዊ ኃይል እና በድርጅታዊ አቅም በመጎልበቱ፣ እንዲሁም ፋኖ ከፍተኛ ድሎች በማስመዝገቡ ሰፊ እውቅናና ተዓማኒነት አግኝቷል። ተፅዕኖው እየሰፋ ሲሄድ የርዕዮተ-ዓለም ግልጽነት እንዲኖረውና የፖለቲካ መስመሩንም እንዲያሳውቅ ከተለያዩ አቅጣጫዎች፣ በተለይም ከዲፕሎማሲው ማኅበረሰብ ጥሪዎች ሲስተጋቡ ቆይተዋል።

    የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ለዚህ ጥሪ ምላስ ለመስጠት ረቂቅ ፍኖተ መርኁን ከወራት በፊት ለአንባብያን አቅርቦ ከማኅበረሰቡ አስተያየት ሲሰበስብ ቆይቷል። እነሆ ዛሬ ከፋኖ አባላትና አመራሮች፣ ከደጋፊዎች እና ከሰፊው ማኅበረሰብ በተገኙ አስተያየቶችና ሃሳቦች የዳበረውን ፍኖተ-መርኅ ለሕዝብ ይፋ የምናደርገው በታላቅ ደስታና የኃላፊነት ስሜት ነው።

    ይህ ፍኖተ-መርህ ከፖለቲካዊ መግለጫ በላይ – ለሕጋዊነት፣ ለተዓማኒነት፣ ለግልጸኝነት፣ ለአንድነትና ለአሳታፊ ፖለቲካ ስትራቴጂያዊ ንድፍ ነው።
    ውጣ ውረድ በበዛበት በዚህ የፋኖ ጉዞ ውስጥ አዲስ ምዕራፍን ከማመላከትም በተጨማሪ፣ የድርጅቱን ግቦች፣ እሴቶች እና ራዕይ በግልፅ ያሳያል።

    ከ50 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን የጨበጡ ተከታታይ መንግሥታት የአማራን ህዝብ ለሥርዓታዊ የዘር ማጽዳት ጅምላ ግድያዎች(ጄኖሳይድ)፣ ለፖለቲካ መገለል እና የባህል መዛባት አጋልጠውት ቆይተዋል። የአማራ ሕዝብ ለሺህ ዓመታት ለሀገር ግንባታ ያበረከተው አስተዋፅዖና የከፈለው መስዋዕትነት እንደ ወንጀል ተቆጥሮ፤ ጀግንነቱን የሚያንቋሽሽ ትርክት ተፈብርኮበታል፡፡ በማግለል የተጀመረው መገፋት ወደ ኅልውና አደጋ ተሸጋግሯል፤ እልቂት፣ መፈናቀል እና ተቋማዊ ጥላቻ የአማራን ሕዝብ ከጥፋት አፋፍ ላይ አድርሶታል።

    በዚህ አውድ የአፋሕድ ፍኖተ-መርህ የፋኖን እንቅስቃሴ የወለደውን ታሪካዊ ኢፍትሃዊነት፣ የፖለቲካ ክህደት እና የአማራን ሕዝብ ድምጽ የማፈን በደል በማሳየት ሊያሳካቸው ቃል ኪዳን የሚገባላቸውን የፍትሕ፣ የአንድነት፣ የሕዝባዊ ሉዓላዊነት እና የሰብአዊ መብት እሴቶች በግልጽ ያስቀምጣል፡፡

    ከተቃውሞ ባሻገር፣ ፍኖተ-መርሁ በዴሞክራሲያዊ አስተዳደር እና በትብብር በመልማት ላይ የተመሰረቱ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፕሮግራሞችን ያካተተ ነው።

    አፋሕድ ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለጭቁንና ጭቆናን ከሚጋፈጡ ማኅበረሰቦች ሁሉ አጋርነቱን ገልጾ ትግሉ የሚመራው በበቀልና በጥላቻ ሳይሆን በእውነትና የወገናቸውን የአማራን ሕዝብ ኅልውና ለማረጋገጥ መሆኑን ነው።

    ይህ ፍኖተ መርህ ለትግሉ ወሳኝ አቅጣጫ አመልካች ሲሆን፣ ለሰፊው የአማራ ህዝብ መሰብሰቢያ ጥላ – ትውልዶችን በፍትሕ እና በተስፋ የሚያገናኝ የጋራ ራዕይ ሆኖ ሲያገለግል፣ ለሰፊው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብም ፋኖ እንዴት ወደ ትጥቅ ትግል እንደተገፋ፣ ንቅናቄው አሁንም ለበቀል ሳይሆን ለፍትህ፣ ለእኩልነት እና በሰላም አብሮ ለመኖር እንደሆነ በግልጽ ያስቀምጣል።

    አፋሕድ ይህን ፍኖተ-መርህ ይፋ በማድረግ፤ በነጻነት፣ በክብር እና በእኩልነት የሚያምኑ ሁሉ ከእውነት ጋር፣ ከፋኖ ጎን፣ በአጠቃላይም በደጀንነት ከአማራ ሕዝብ ጋር እንዲቆሙ ጥሪውን ያቀርባል። ከፊታችን ያለው መንገድ የትግል ብቻ ሳይሆን ስልጣኔን እንደገና የመገንባት እና ፍትሓዊት የተባበረች ኢትዮጵያን የመፍጠር ነው።

    የአፋሕድን ፍኖተ መርህ ለማንበብ፤ https://thevoiceoffano.com/storage/2025/10/AFPO-Manifesto_Bilingual_20October2025.pdf ን ይጠቀሙ

    “ክብር እና ሞገስ ለሰማዕታት!!!

    ድል ለአፋሕድ እና የአማራ ፋኖ ሁሉ!!!
    ድል ለአማራ ሕዝብ!!!
    ድል ለኢትዮጰያ ሕዝብ!!!
    /
    ጥቅምት 12፣ 2018 ዓ.ም።

  • በጨጨሆ መድሀኒዓለም፥በመንዝ ፋኖ ድል ተቀዳጀ!

    አፋህድ የጥቅምት 10፣ 2018 ዓ.ም የአውደ ውጊያ ውሎ–በጨጨሆ መድኃኒዓለም እና መንዝ ፋኖ ድል ተቀዳጅቷል፣ የ8ኛው ዙር ፋኖ ሰልጣኞች በሸዋ ተመረቁ!!!
    /
    ጥቅምት 10፣ 2018 ዓ.ም።
    /
    የአፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር፣ ጥቅምት 10፣ 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት አንስቶ ጎንደር እና ወሎን በሚያገናኘው የጨጨሆ መስመር ላይ ከአገዛዙ ጦር ጋር እልህ አስጨራሽ ውጊያ አድርጎ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶበታል።

    የአገዛዙ ጦር ከአራት ቀን በፊት በወገን ጦር ላይ አፈና ለመፈጸም ጥረት አድርጎ ከፍተኛ የሆነውን ኃይሉን አጥቶ ወደተነሳበት ምሽጉ በሽንፈት የተመለሰ ሲሆን፣ ዛሬ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 ዓ.ም ከመጥፋት የተረፈውን ጦሩን ለዳግም ዘመቻ በማሰማራት፣ በቀጠናው በፋኖ ከበባ ውስጥ ካሉ ኃይሎቹ መካከል አርብ ገበያ ከሚገኘው 77ኛው ክፍለ ጦሩ አንድ ሬጅመት፣ እንዲሁም ከነፋስ መውጫና ጎብጎብ ካለው 92ኛው ክፍለ ጦሩ አንድ ሬጅመት በወገን ጦር ላይ የቁጥር እና የመሣሪያ የበላይነት ይዞ የዘመተ ቢሆንም ያሰበውን ማሳካት ሳይችል ቀርቷል።

    በጀግኖቻችን እና በአገዛዙ ጦር መካከል ጨጨሆ መድኃኒዓለም፣ ጋንጋ፣ ጨጨሆ ጤና ጣቢያ ፣ አጓት ውሃ፣ ጊጦ ተራራ ላይ እልህ አስጨራሽ የጨበጣ ውጊያ ሲደረግበት ውሎ፣ ጠላት የማሰው ምሽግ መቀበርያው ሆኗል ።

    በዚህ ውጊያ የሰመዓቱ አርበኛ ከፍያለው የእጅ ስራ የሆነው ጀግናው ገብርዬ ክፍለ ጦር ፣ጀግናው የአንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር ፣ ጀግናው የተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር እና የ206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ጥምር ኃይል ወታደራዊ ትስስር ፈጥረው ጠላትን ሽንፈት አከናንበውታል።

    አገዛዙ በዙ -23 ፣ ሞርተር እና ዲሽቃ የታገዘ ውጊያ ቢያደርግም፣ በዕለቱ ውጊያዎች :-

    — በጠላት በኩል 38 ሙት ፣
    — 72 ቁስለኞች እንደደርስበት የታወቀ — 12 የነፍስ ወከፍ ክለሽ እና በርካታ የክላሽና የዲሽቃ ተተኳሾች ምርኮ ሆነዋል።

    በዕለቱ የውጊያ ውሎ በጠላት በግዴለሽነት እና በበቀል ስሜት ወደ ህዝብ በሚተኮሱ የዙ-23፣ ሞርታሮች እና ዲሽቃ አረሮች በንፁሃን ገበሬዎች እና ንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት ደርሷል። ዝርዝር መረጃው በሂደት ይፋ ይሆናል።

    ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአፋህድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ለ8ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን መደበኛ የፋኖ እጩ ታጋዮችን ጥቅምት 9 ፣ 2018 ዓ.ም አስመርቋል።

    የአገዛዙ ጦር ጥቅምት 10፣ 2018 ዓ.ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከመንዝ ቀያ ወረዳ ዘመሮ ከተማ፣ እንዲሁም፣ ከመንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ በሁለት ግንባሮች ተቀናጅቶ በወገን ጦር ላይ በሌሊቱ ከበባ ለመፈፀም የተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ የአፋህድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር አካል የሆነው ጀግናው ምኒልክ ክፍለ ጦር ከበባውን ሰብሮ በመውጣት እና የመልሶ ማጥቃት በመፈፀም ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል።

    በውጊያው ቀጠና ከዘመሮ ከተማ ወደ ክምር ድንጋይ የተንቀሳቀሰው 112ኛው አየር ወለድ ክፍለ ጦር፣ በጀግናው ምኒልክ ክፍለ ጦር የደፈጣ ጥቃት ሲፈፀምበት፣ ከወገሬ ከተማ ተነስቶ አድማሱን በማስፋት ወደ ጦል ከተማ ተንቀሳቅሶ የወገንን ኃይል ለመበተን ሙከራ አድርጎ ሳይሳካለት ቀርቷል።

    ከንጋቱ 11:30 ላይ ጀምሮ በሁለቱም ግንባሮች በተካሄደው ውጊያ ሞርተርን ጨምሮ ዙ-23 እና ሌሎች የቡድን መሳሪያዎች የተጠቀመ ሲሆን፣ ከወገን ጦር ይልቅ በንፁሃን ላይ ጉዳት አድርሷል። ይህ መግለጫ እስከሚወጣበት ግዜ ድረስ ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን፣ በጠላት ላይ የደረሰው ጉዳት እና በሲቭሎች ላይ የደረሰው ጉዳት ዝርዝር በቀጣይ ቀናት ይፋ ይሆናል።

    የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ፣ አገዛዙ በልዩ ሁኔታ አሰልጥኖ በተለይ የአዲስ አበባ በር በሆነው የሸዋ ቀጠና ካሰፈረው በርካታ የአየር ወለድ ኮማንዶ ጋር ከሚያደርገው የእለት በእለት ውጊያ ጎን ለጎን፣ ታጋዮችን አሰልጥኖ በማስመረቅ ሰፊ ልምድ ያካበተ ተቋም ሲሆን፣ በእዝ ደረጃ ለተከታታይ 8 ጊዜ በሺህዎች የሚቆጠሩ ፋኖዎችን አሰልጥኗል። ስልጠናውም በቀጣይነት ተጠናክሮ ይቀጥላል።

    ክብር እና ሞገስ ለሰማዕታት!!!

    ድል ለአፋህድ እና የአማራ ፋኖ ሁሉ!!!
    ድል ለአማራ ህዝብ!!!
    ድል ለኢትዮጰያ ህዝብ!!!
    /
    ጥቅምት 10፣ 2018 ዓ.ም።

  • የአፋህድ የሀዘን መግለጫ!

    የአፋህድ የሐዘን መግለጫ!

    በክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ህልፈት ከልብ አዝነናል!
    /
    ጥቅምት 10፣ 2018 ዓ.ም።
    /
    ከኢትዮጰያዊያን ኃይማኖት አባቶቻችን መካከል ጉልህ ስፍራ ያላቸውን የክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ህልፈት የሰማነው በታላቅ ሀዘን እና ድንጋጤ ነው።

    የክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በህይወት ዘመናቸው ለእምነታቸው ትጉ ፣ፅኑ፣ ቀናኢ እና በመንፈሳዊ ትምህርታቸው እና ብቃታቸው ደግሞ የላቀ ደረጃን የተጎናፀፉ አባት ነበሩ።

    በዓለማዊ ጉዳዮች ደግሞ፣ ሀገር ወዳድ፣ የፍቅር እና ወንድማማችነት አስተማሪ፣ ሰው አክባሪ፣ ለችግረኞች ደራሽ፣ ለባለግዜዎች ማጎብደድን የማይወዱ የዘመናችን ዋርካ ነበሩ።

    የክብር ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ለታሪክ ትተውት ካለፏቸው ጉልህ አሻራዎች መካከል፣ የኢትዮጰያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ህጋዊ እውቅና እንዲያገኝ እና እስላማዊ ባንኮች እንዲቋቋሙ ያበረከቱት አስተዋፅኦን መጥቀስ ይቻላል። ሌሎች ብዙዎችም አሉ።

    የአባታችንን መልካም ስራዎች ሁሉ ፈጣሪ እንዲቀበልላቸው እና ምንዳቸውንም ጀነተል ፊርደውስ እንዲያደርግላቸው፣ እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸውን እንዲያፅናናላቸው እንመኛለን።

    ድል ለአፋህድ እና የአማራ ፋኖ ሁሉ!!!
    ድል ለአማራ ህዝብ!!!
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
    /
    ጥቅምት 10፣ 2018 ዓ.ም።

  • “አገዛዙ ሲደነግጥ የሚያደርገው የተለመደ ማጭበርበር ነው” አርበኛ እስክንድር ነጋ!

    እስክንድር ነጋ።
    ///

    በሌለ ድርድር ፋኖን መከፋፈል አይቻልም!!!
    /
    ጥቅምት 07፣ 2018 ዓ.ም።
    /
    “የአማራ ክልል መንግሥት ተብዬው ከፋኖ ጋር ድርድር እያደረግኹ ነው” ያለውን አስመልክቶ፣ የብልፅግና ዲጂታል ሚሊሻ አንዳንድ የአፋህድ አመራሮችን ስም በሀሰት እያነሳ ይገኛል።

    የክልሉ መንግሥት ከፋኖ ጋር እውነት እየተደራደረ ከሆነ፣ የአደረጃጀቱን ስም ይፋ ሊያደርግ ይገባል። ከክልሉ መንግሥት ጋር እየተዳደራደረ ያለ የፋኖ አደረጃጀት ካለ፣ እውነታውን ለህዝብ ይፋ ማድረግ ይገባዋል።

    ከአካሄድም አኳያ ብናየው፣ የብልፅግና እና የፋኖ ጦርነት ከእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት አይብስም። እስራኤል እና ሃማስ ድርድር ሲያደርጉ ግን በሚስጥር አልተደራደሩም። የፋኖ እና የብልፅግና ድርድርም በምንም መሥፈርት ሚስጥራዊ የሚሆንበት ምክንያት የለም ። እንዲያውም፣ በተቃራኒው፣ ድርድር ካለ መላ ኢትዮጵያዊያን ማወቅ ይፈልጋሉ። እውነታው ይነገራቸው።

    እስካሁን በተግባር እንዳየነው ግን፣ ብልፅግና ድርድርን የሚያነሳው ለሰላም ብሎ ሳይሆን ፋኖን ለመከፋፈል አጄንዳ መስጠት ሲፈልግ ብቻ ነው። አንድ ግዜ ሞክሮት ከሽፏል። አሁን ለሁለተኛ ግዜ እየሞከረው ነው። ይህም ይከሽፋል።

    እስክንድር ነጋ፣
    ከአፋህድ።