
አፋህድ ጥቅምት 06፣ 2018 ዓ.ም የአውደ ውጊያ ውሎ— የአገዛዙ ጦር ሙት እና ቁስለኛ ሆነ፣ መኮይ ከተማ ተከባለች!!!
/
ጥቅምት 06፣ 2018 ዓ.ም።
/
የአፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ 206ኛ ኮር፣ ከትላንት ሌሊት አንስቶ እስከ ዛሬ፣ ፣ጥቅምት 6፣ 2018 ዓ.ም ድረስ በጨጨሆ እና ጋንጋ ላይ ከባድ ውጊያዎችን ሲያደርግ ውሏል።
የጠላት ጦር ከታች ጋይት እና ጎብጎብ ብዛት ያለው ኃይል አሰባስቦ ወደ ውጊያ ቢገባም፣ የነበልባሎቻችንን ምላሽ መቋቋም ተስኖት፣ ከሙት እና ጉዳት የተረፉትን የመከላከያ፣የአድማ ብተና፣ የሚሊሻ እና የፖሊስ አባላቱን ይዞ ምሽጉ ወዳደረጋቸው ታች ጋይንት እና አርብ ገበያ ከተሞች በሽንፈት ተመልሷል።
በአውደ ውጊያዎቹ 25 ሙት እና ከ40 በላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ቁስለኞች እንደነበሩ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ግዜ ታውቋል። አጠቃላይ መረጃው በቀጣይ ቀናት ይፋ ይሆናል።
በሌላ አውደ ውጊያ፣ ወደ አጋጥ የተንቀሳቀሰውን የጠላት ኃይል የጀግናው ገብርዬ ክፍለ ጦር አካል የሆኑ ሁለት ብርጌዶችን ለማፈን ቢሞክርም፣ ከጠዋቱት 12:00 ሰዓት ጀምሮ በነበረው ውጊያ በጀግናው ሠራዊታችን ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል።
በዚህ አውደ ውጊያ ጠላት በደረሰበት ጉዳት ተበሳጭቶ በሲቪሎች ላይ ባደረሰው የበቀል እርምጃ በቀበሌ 12፣ ልዩ ስሙ “ወንቢ” በሚባል ቦታ ከእርሻ ማሳቸው በስራ ላይ የነበሩ አርሶ አደሮችን በግፍ ረሽኗል። ወንጀሉን የሰብዓዊ መብት ተቋማት እንዲያጣሩ እንጠይቃለን።
የአፋህድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር አካል የሆነው ጀግናው አስቴጎማ ተራራ ክፍለ ጦር፣ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ ይፋት አውራጃ፣ በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ የአገዛዙ ጦር እስካለበት ድረስ በሰርጎ ገብ ኦፕሬሽን ሰርገው በመግባት ከጠላት ወታደሮች ጋር በጨበጣ ውጊያ ተናንቀው ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውበታል።
ከጥቅምት 2 እስከ 6፣ 2018 ዓ.ም ለተከታታይ አራት ቀናት ተፋፍሞ በሚገኘው አውደ ውጊያ፣ በይፋት አውራጃ፣ አንፆኪያ ገምዛ ወረዳ የምትገኘው መኮይ ከተማ በጀግናው ሠራዊታችን ከበባ ውስጥ ገብታ የአገዛዙ ጦር በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ይገኛል።
ጀግናው አስቴጎማ ተራራ ክፍለ ጦር በመኮይ ከተማ ዙሪያ ባሉት በአርባ አራቱ ቀበሌ፣ በወበሻ ቀበሌ፣ በመቅደሳ ቀበሌ፣ በ04 ቀበሌ፣ በ05 ቀበሌ ገዢ መሬቶችን በመያዝ የጠላት ጦር ገና ከምሽጉ ብቅ ሲል ከባድ የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ዋጋ እንዲከፍል እያደረጉት ይገኛል።
ውጊያው ለቀጣይ ቀጠናት የሚቀጥል ሲሆን፣ በማጠቃለያው በሚኖረን መግለጫ በጠላት ላይ የደረሰውን ጉዳት በዝርዝር እናቀርባለን።በዚህ መግለጫ፣ ለአብነት እንዲሆን አገዛዙን ከድቶ ፋኖን የተቀላቀለ ኦሮምኛ ተናጋሪ የኮማንዶ አባል ምስልን ከእነ ዘመናዊ ስናይፐሩ አቅርበናል። ስርዓቱ የሚተማመነው በእንደዚህ ዓይነቱ ወታደር ቢሆንም፣ አሁን እየከዳው ይገኛል።
በሌላ አውደ ውጊያ፣ ዛሬ፣ ጥቅምት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት 30 በአገዛዙ የ 112ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ ክፍለ ጦር በመንዝ ቀያ ወረዳ፣ ከዘመሮ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የአመጃ ቀበሌ፣ ልዩ ስሙ “ጫት ውሃ” በተባለ ቦታ የአፄ አምደ ጽዮን ኮር አካል የሆነው ጀግናው ምኒልክ ክፍለ ጦር በፈፀመው የደፈጣ ጥቃት ከፍተኛ ድል ተቀዳጅቷል።
መነሻውን ከዘመሮ ከተማ አድርጎ ወደ ዘረት በመንቀሳቀስ ላይ የነበረው ጠላት በጀግኖቻችን በተፈፀመበት ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት በመሆኑ፣ ተጨማሪ ኃይል ከመሃል ሜዳ እንዲላክሎት ጠይቆ፣ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ግዜ ድረስ ውጊያው እንደቀጠለ ይገኛል። ውጤቱ በቀጣይ ቀናት ይፋ ይሆናል።
ትግሉ ተፋፍሞ ይቀጥላል።
ክብር እና ሞገስ ለሰማዕታት !!!
ድል ለአፋህድ እና የአማራ ፋኖ ሁሉ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
ድል ለኢትዮጰያ ህዝብ!!!
/
ጥቅምት 06፣ 2018 ዓ.ም






You must be logged in to post a comment.